ብሎግ ማለት ምን ማለት ነው?

melese abraham
Note by melese abraham, updated more than 1 year ago
melese abraham
Created by melese abraham over 4 years ago
26
0

Description

ብሎግ የኢንተርነት ዓይነት ነው። ብሎግ የሚለው ቃል በኢንተርነት በመረብ ላይ የተዘረጋ የግል ማስታዎሸ ወረቀት ማለት ነው። በዚህ ማስታወሻ ገጽ ላይ የተለያዩ ርዕሶችን ወይም ፋይሎችን መመዝገብ ይቻላል። እያንዳንዱ ርዕስ ራሱን የቻለ የብሎግ ገጽ ወይም ማስታወሻ ወረቀት ይይዛል። ብሎግ ዘመናችን ከፈራው የድጂታል የሆነ ዘመናዊ መሣሪያ ዓይነት ሲሆን ብሎግ በራሱ ገጽ ለተመዘገበ ግለሰብ፣ በተመሳሳይ ዓላማ ላይ የተመሠረተ አንድ ቡድን ወይም ኅብረተሰብ ሁሉ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችን መቀበልና ማስተላለፍ የሚቻልበትን መንገድ ያመቻቻል። በአንድ የማስተዋሻ ገጽ ላይ አንድ ርዕስ ብቻ ቢይዝ ይመረጣል። ለምሳሌ ያህል
Tags

Resource summary

Page 1

ባዛሬው ምሽት ስብሰባችን የምንነጋገርባቸው በሚከተሉት ርዕሶች ላይ እንነጋገራለን 1. ብሎግ ማለት ምን ማለት ነው? 2. ብሎግ በመማርና ማስተማሩ ሂደት ላይ ምን አገልግሎት ይሰጣል? 3. የጥያቄና መልሶች።· የስፖርት ገጽ · የሙዚቃ · የፖለቲካ · የሳይንስ · የኢዲዩ ገጽ · የቋንቋ ገጾች ለየራሳቸው አንድ የመገናኛ መረብ ወይም መድረክ (የመገናኛ መርቦችን) ይይዛሉ ማለት ነው። እኛ ዛሬ የምናተኩረው ቋንቋን በተመለከተ ይሆናል። ብሎግ በመማርና በማስተማሩ ሂደት ውስጥ ምን ሚና ይጫዎታል? ብሎግ ለአጠቃቀም ቀላል እንደመሆኑ መጠን በዘመናችን "ስማርት ፎኖች"ን በመጠቀም በርከት ያሉ ሥራዎችን መሥራት የቻላል። · ተማሪዎች በጻፍነው ሐሳብ ላይ ሓሳብ እንዲጸጡ ማድረግ። · የጻፍነው ጽሑፍ በቋሚነት ደረጃ እንዲጠበቅ ማድረግ። · የጻፍነውን ማንኛውንም ጽሑፍ ይፋ እንዲዎጣ ወይም ለፈለግነው ሰው ብቻ እንዲደርስ "ፖስት" ወይም ማስተላለፍ እንችላለን። · ፖስት - ማንኛውንም ልናሳትፍ የፈልግነውን ጽሑፍ ለግለሰብም ሆነ ማህበረሰብ የምናሳትፍበት ዜዴ ነው። ፖስት= ሸር የሚለውን የእንጊሊዝኛ ቃል በዚህ ገጽ ላይ ይወርሳል። በሌላ አባባል ፖስት የሚለው ቃል በዚህ ገጽ ላይ ሌሎችን እናሳትፍ የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ ነው። እንዴት አድርገን ለሎች ተሳታፊዎች ማሳተፍ እንደምንችልና የተሳፊዎቻችን ሐሳብ በአንድ ገጽ ላይ ማሰባሰብ እንደምንችል የሚያደርግ መድረክ ወይም የመገናኛ ዘዴ ነው። ማስታወቅ የፈለግነውን ነገር ሁሉ በመጽሑፍ ማሳተፍ ችሎታውን አውርሶናል። ብሎግ ለመምህራን የሚሰጠው አገልግሎት ምንድነው? 1. የጋራ ዕውቀትን ማካበቻ - እውቀታችን በአንድ ላይ ሆነን በየቀኑ በምናደርጋቸው የትምህርት ሥራ ሙከራዎች ከፍተኛ የሆነ ዕቀቶችን መለዋወጥ እንችላለን ማለት ነው። 2. የግል ዕውቀትን ማሳተፍ - እያንዳንዱ የሚያውቀውን ዕውቀት በራሱ ተወስኖ እንዳይቀር ሲፈልግ ዕውቀቱን ወደ ወል እውቀት ለመቀየር ሲፈልግ ለሁሉ ሰው ያሳትፋል። አንባቢያን ካነበቡ በኋላ ምክራቸውንና ገንቢ ወይም አፍራሽ ሒስ በማቅረብ የዕውቀቱ ተሳታፊ ይሆናሉ። ለምሳሌ ያህል እኛ የአማርኛ ትምህርት እንዲስፋፋ የጋራ መፍትሔዎችን ለመፈለግ ያመቸን ዘንድ አንድ ገልሰብ በሚያቀርበው ጥያቄ እያንዳንዳችን በምንሰጠው መልስ የጋራ ዕውቀትን መገብየት እንችላለን ማለት ነው። የዚህ ዓይነት አሠራር ለቋንቋችን እድገትና ለሥራችን ጥራት ያስገኛል የሚል እምነት አለኝ። ከሌሎች ግለሰቦች ያገኜነውን ዕውቀት ሁላችን እንድናውቅ ያደርገናል። 3. ለማስተማሪያ ጠቃሚ የመሰሉንን የኢንተርነት ገጽ አድራሻዎችን፣ ቢዲዮ፣ ፎቶ ግራፎችንና የተለያዩ የትምህርት መረጃ ዶክመንቶችን መመዝገብ ይቻላል። 4. ከሌሎች ዓለም አቀፍ መምህራን (ሙያተኞች) ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ግለሰቦች ጋር ግንኙነት ማድረግ አዳዲስ ሐሳቦችን ለመለዋወጥ እንድንችል ይረዳናል። ጥሩ የመመዘኛ ወጤት መገምገም · ኦርጅናል(ዋና)- ከራሳችን የፈለቁ ማለትም የሆነ ከሌላ ሰው ያልተወሰዱ ጽሑፎችን መስቀመጥ ማስቻሉ · አዳኢስ ነገሮችን በቅጽበት መቀበልና ማስተላለፍ መቻላችን። · እኛ በአስተዳደር ደረጃ የምናዝበት ራሳችን ገጽ መፍጠራችን የመሳሰሉትን ጥቅም ይሰጣል። ብሎግ ለተማሪዎች የሚሰጠው አገልግሎት ምንድነው? 1. በክፍል ደረጃ ተማሪዎቻችን የራሳቸውን ብሎግ በመክፈት እርስ በእርሳቸው ዝግ ብሎግ። 2. የክፍል ተማሪዎችንና የክፍሉን መምህራ የሚያሳትፍ ዝግ የብሎግ ዓይነት ነው። 3. ብሎጉ ለሁሉም ሰዎች በግባትና አሳባቸውን መስጠት የሚችሉበት ይችላል። የት/ቤት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ሆነ ዓለም አቀፋዊ ደርጃ በተማሳሳይ ርዕስ ላይ የሚወያዩበት የማስታወሻ መክፈት ይችላሉ። ብሎግ ለት/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት ምንድነው? ትምህርት ቤቱ የራሱ የሆነ ብሎግ መፍጠር ይችላል። ይህ ብሎግ የትምህርት ቤቱ መምህራን ብቻ የሚሳተፉበት ወይም ሌሎች ዓለማቀፍ መምህራን እንዲሳተፉበት ማድረግ ይችላል።

Show full summary Hide full summary

Similar

GCSE AQA Physics - Unit 3
James Jolliffe
GCSE AQA Chemistry - Unit 3
James Jolliffe
GCSE AQA Physics - Unit 3
Jeffrey Piggott
Leyes de Newton
Yoselin Sánchez
Leyes de newton
KELED ROSAS
Chapter 3
Ryan Tram
CCNA Answers – CCNA Exam
Abdul Demir
Chapter 4
Ryan Tram
Chapter 2
Ryan Tram
Chapter 8
Ryan Tram